በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር RE-LT/HT/HO/08/2019
ሕዳሴ ቴሌኮም አክሲዮን ማህበር የተለያዩ የዳታ ሴንተር ሴትአኘ እና ኔትወርክ ግንባታ በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፍኬት እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘዉን የዳታ ሴንተር ሴትአኘ እና ኔትወርክ ግንባታ ጨረታ ሰነድ ግንቦት 26 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡00 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -10፡30 ድረስ ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ ዋናዉ መ/ቤት ደብረ ዘይት መንገድ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት ከበእምነት ምግብ ቤት ገባ ብሎ በሚገኘው ቤተሳይዳ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመቅረብ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለዳታ ሴንተር ሴትአኘ እና ኔትወርክ ግንባታ ጨረታ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሽህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ክፍያ ማስያዣ /C.P.O/ ለሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ሐምሌ 2 ቀን 2011 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ቢሮ ቁጥር 306 ሲሆን፣ ተጫራቾች ሰነዳቸዉ ከዚህ በሚከተለዉ መልኩ ማቅረብ አለባቸዉ፡-
- አንድ ዋና /Original/ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሻል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጎ ፤
- አንድ ቅጂ /Copy/ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሻል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጎ ፤
- ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ በሰም የታሸገ መሆን አለበት፡፡
- በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ የመክፈቻ ቀን ሐምሌ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 307 የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0118-55 11 78 ፋክስ ቁጥር 0114-663649 መጠቀም ይችላሉ፡፡
- ሕዳሴ ቴሌኮም አ.ማ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡